የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ዜጎች ብክለት የተገኘበትን የኔስሌ የሕፃናት ወተት እንዳይጠቀሙ አስጠነቀቀ

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ዜጎች ብክለት የተገኘበትን የኔስሌ የሕፃናት ወተት እንዳይጠቀሙ አስጠነቀቀ
ባለሥልጣኑ “ናን ስፔሻል ፕሮ ኤች ኤ 0-12” (NAN Special Pro HA 0-12) የተሰኘው የኔስሌ የሕፃናት ወተት ምርት በባክቴሪያ መበከሉ ስለተረጋገጠ፤ ኅብረተሰቡ ምርቱን እንዳይጠቀም በማሳሰብ ከገበያ እንዲወጣ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ብክለት የተገኘበት ምርት ዝርዝር መረጃ፦
▪የምርት ስም፦ NAN Special Pro HA 0-12
▪የባች ቁጥር ፦ 51660742F3
▪የምርት ቀን፦ እ.አ.አ ሰኔ 15 ቀን 2025
▪የሚያበቃበት ቀን፦ እ.አ.አታህሳስ 15 ቀን 2026
▪ክብደት፦ 800 ግራም
ምርቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሕጋዊ መንገድ ያልተመዘገበና ለገበያ እንዲቀርብ ፈቃድ ያልተሰጠው መሆኑን የገለፀው ባለሥልጣኑ፣ በሕገ-ወጥ መንገዶች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አስገንዝቧል። በእጃቸው የሚገኝ ወይም ገበያ ላይ የተመለከቱ ሰዎች ምርቱን ለይተው እንዲያስቀምጡና ወዲያውኑ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠይቋል።
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በኩባንያው ሌሎች ምርቶች ላይም ምርመራ እያካሄደ መሆኑንና ተጨማሪ መረጃ ሲገኝ ለሕዝቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X