ማሊ የብሔራዊ እርቅ አካል የሆኑ 341 የቀድሞ አማፂያንን ወደ ጦር ሠራዊቱ ቀላቀለች
19:45 09.01.2026 (የተሻሻለ: 19:54 09.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ማሊ የብሔራዊ እርቅ አካል የሆኑ 341 የቀድሞ አማፂያንን ወደ ጦር ሠራዊቱ ቀላቀለች
በማሊ ቲምቡክቱ እና ታውዴኒት ክልሎች ትጥቅ የማስፈታት፣ የመበተን እና ወደ ማኅበረሰቡ የመቀላቀል ጥረት በይፋ መጀመሩን የማሊ ጦር ኃይሎች አስታውቋል።
የክልል ገዥዎች በተገኙበት እና የብሔራዊ ኮሚሽኑ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ባለሥልጣናት የተሳተፉበት የቲምቡክቱ ሥነ-ሥርዓት፤ ለሀገራዊ እርቅ ሂደቱ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ጦሩ ገልጿል።
🪖 መርኃ-ግብሩ የማሊን ጦር ለማጠናከር፣ ሥራ አጥነትን ለመቀነስ እና የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመግታት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህም 341 የቀድሞ ተዋጊዎች በሁለተኛ ደረጃ ወታደርነት ወደ ማሊ ጦር ይቀላቀላሉ። ባለሥልጣናት ሂደቱ ሁሉንም ያካተተ እና በማሊ ማኅበረሰብ እሴቶች፣ በዓለም አቀፍ የሰብዐዊ መብት ሕጎች እና በሰብዓዊ መብቶች ላይ የተመሠረተ መሆኑን ገልጸዋል።
በቲምቡክቱ የተከናወነው ምዕራፍ በሀገሪቱ ሲካሄዱ የቆዩ ተመሳሳይ ኦፕሬሽኖች ማጠቃለያ መሆኑን የማሊ ጦር አስታውቋል። ባለሥልጣናት ለዚህ ተነሳሽነት ስኬት የታጠቁ ቡድኖች መሪዎች እና የአካባቢው ማኅበረሰቦች ሙሉ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

