የዲጂታል አድራሻ ጠቋሚ ሥርዓት በስምንት ከተሞች ተግባራዊ ተደረገ
19:21 09.01.2026 (የተሻሻለ: 19:24 09.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የዲጂታል አድራሻ ጠቋሚ ሥርዓት በስምንት ከተሞች ተግባራዊ ተደረገ
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በአዳማ፣ ሐረር፣ ጅማ፣ ደብረ ብርሃን፣ ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ኮምቦልቻ እና ቢሾፍቱ ከተሞች የዲጂታል አድራሻ ሥርዓትን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል።
የሥርዓት ልማቱ ተጠናቆ በአሁኑ ወቅት የመስክ ሙከራ እየተደረገ ሲሆን፣ በቅርቡ ተመርቆ ለነዋሪዎች እና ለጎብኚዎች አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተጠቁሟል።
ኢንስቲትዩቱ ለዚሁ አገልግሎት የሚውል የተሻሻለ የሞባይል መተግበሪያ በቅርቡ ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብ ገልጿል።
ዘመናዊ የአድራሻ ሥርዓት በከተሞች የሚገኙ ቤቶችን እና ተቋማትን በቀላሉ በዲጂታል ካርታ ለማግኘት የሚያስችል ሲሆን ለከተማ አገልግሎት መሳለጥ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X