በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በነጠላ አሃዝ ተመዘገበ
19:05 09.01.2026 (የተሻሻለ: 19:14 09.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በነጠላ አሃዝ ተመዘገበ
የሀገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በታኅሣሥ ወር ወደ 9.7 በመቶ ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል።
በተጠናቀቀው የታህሳስ ወር የተመዘገብው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ኅዳር ወር ጋር ሲነፃፀር የ0.3 በመቶ ቅናሽ የታየበት መሆኑን አገልግሎቱ ይፋ አድርጓል።
በዚህም፦
◻ የምግብ እና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች የዋጋ ግሽበት 9.8 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የአትክልት፣ የሥጋ፣ የጥራጥሬ፣ የወተት ተዋጽኦዎች እና የቅባት እህሎች ዋጋ መጨመር በዋናነት አስተዋጽኦ አድርገዋል።
◻ ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች እና አገልግሎቶች የዋጋ ግሽበት 9.6 በመቶ ደርሷል፡፡
ሆኖም ትራንስፖርት (17.6 በመቶ)፣ የተለያዩ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች (21.5 በመቶ)፣ እንዲሁም የግንኙነት (13.9 በመቶ) ዘርፎች ከፍተኛውን ጭማሪ ማሳየታቸውን የአገልግሎቱ መረጃ አመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X