ኢራን በሀገሪቱ ለተቀሰቀሰው አለመረጋጋት አሜሪካንና እስራኤልን ወቀሰች
18:41 09.01.2026 (የተሻሻለ: 18:44 09.01.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢራን በሀገሪቱ ለተቀሰቀሰው አለመረጋጋት አሜሪካንና እስራኤልን ወቀሰች
የኢራን ከፍተኛ ብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ አሜሪካ እና እስራኤል በሀገሪቱ ተቀስቅሶ ወደ አመጽ የተቀየረውን ተቃውሞ አስተባብረዋል ሲል ከሷል።
እ.አ.አ በታህሳስ 2025 መጨረሻ አካባቢ በገንዘብ ምንዛሬ መዋዠቅ እና በኑሮ ውድነት ምክንያት የጀመረው ተቃውሞ፤ ብዙም ሳይቆይ ወደ ግጭት እና ሁከት የተቀየረ ሲሆን በበርካታ ከተሞች በጸጥታ ኃይሎች እና በተቃዋሚዎች ላይ የሕይወት መጥፋት አስከትሏል።
ምክሩ ቤቱ የዶናልድ ትራምፕን የቅርብ ጊዜ መግለጫዎች በመጥቀስ፤ ተቃውሞዎቹ "በጽዮናውያን ጠላት ቁጥጥር እና እቅድ ስር" ያሉ ደግሞም ኢራን እንዳትረጋጋ ለማድረግ የተጠነሰሱ የአሜሪካና እስራኤል ተልዕኮ አካል ናቸው ብሏል።
የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ብሮድካስት ያወጣው ምስል ሐሙስ በቴህራን እና በሌሎች ከተሞች የተካሄዱ ተቃውሞዎችን ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X