የሩሲያ ጦር በዲኔፕሮፔትሮቭስክ ክልል የሚገኝ ቁልፍ ስፍራን እንዴት በቁጥጥር ስር እንዳዋለ መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ
17:56 09.01.2026 (የተሻሻለ: 18:04 09.01.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ጦር በዲኔፕሮፔትሮቭስክ ክልል የሚገኝ ቁልፍ ስፍራን እንዴት በቁጥጥር ስር እንዳዋለ መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው ምስል፤ የሩሲያ ጦር ብራትስኮዬ የተሰኘችውን ታክቲካዊ ጠቀሜታ ያላት ሰፈራ ነፃ ሲያወጣ ያሳያል። የዚህች ቦታ በቁጥጥር ስር መዋል ከጋይቹር ወንዝ በስተምዕራብ ያለውን ይዞታ የሚያሰፋና ለቀጣይ ግስጋሴዎች መንገድ የሚከፍት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የጥቃት ፈፃሚ ክፍሎቹ ከ9 ስኩዌር ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍን የጠላት መከላከያ ይዞታን የተቆጣጠሩ ሲሆን ቀደም ሲል በዩክሬን ኃይሎች ተይዘው የነበሩ ከ170 በላይ ሕንፃዎችን ማጽዳታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በጥቃቱ ከ10 በላይ ሮቦቲክ ፕላትፎርሞች እና "ባባ ያጋ" የተሰኙ ሄክሳኮፕተር ድሮኖችን ጨምሮ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ መድረሱ ተገልጿል።
በዲኔፕሮፔትሮቭስክ ክልል የሚገኘው የዚህ ስፍራ ነፃ መውጣት የተነገረው ሐሙስ ዕለት ሲሆን የሩሲያ ጦር የሩሲያን ክልሎች ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የመከላከያ ቀጣና እየፈጠረ መሆኑ ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X