ጋና ለመንገድ ግንባታ የሚውል የመጀመሪያውን የሀገር ውስጥ የመሠረተ ልማት ቦንድ ልታወጣ እንደሆነ ተገለጸ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱጋና ለመንገድ ግንባታ የሚውል የመጀመሪያውን የሀገር ውስጥ የመሠረተ ልማት ቦንድ ልታወጣ እንደሆነ ተገለጸ
ጋና ለመንገድ ግንባታ የሚውል የመጀመሪያውን የሀገር ውስጥ የመሠረተ ልማት ቦንድ ልታወጣ እንደሆነ ተገለጸ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.01.2026
ሰብስክራይብ

ጋና ለመንገድ ግንባታ የሚውል የመጀመሪያውን የሀገር ውስጥ የመሠረተ ልማት ቦንድ ልታወጣ እንደሆነ ተገለጸ

የጋና መንግሥት ለመንገዶች እና የማቆራራጫ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል 10 ቢሊዮን ሴዲ ወይም 935 ሚሊዮን ዶላር ያህል ገንዘብ ለማሰባሰብ ማቀዱን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ምንጮችን ጠቅሰው ዘግበዋል።

🟠 የቦንዱ አወቃቀር፦ እንደ ዘገባው ከሆነ በሁለት ዙር በሚከናወነው ሽያጭ 5 ቢሊዮን ሴዲ በ2026 የመጀመሪያ እና ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ለገበያ ይቀርባል። ቦንዱ ረዘም ያለ የክፍያ ጊዜ ይኖረዋል።

🟠 የፋይናንስ ሞዴል፦ የዚህ ዕቅድ ዋነኛ መለያ ፕሮጀክቶቹ ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደራቸው ነው። በዋናነት በኤሌክትሮኒክ የጎዳና ላይ ቀረጥ የሚሰበሰብ ሲሆን ዓላማውም በሀገሪቱ የዕዳ ጫና ላይ ተጨማሪ ሸክም እንዳይፈጠር ማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።

🟠 ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ፦ እርምጃው በሀገሪቱ የታየውን የተሻሻለ የኢኮኖሚ ሁኔታ መሠረት ያደረገ ነው። በአሁኑ ወቅት የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ሲሆን የጋና ገንዘብ (ሴዲ) የመግዛት አቅምም እየጠነከረ መጥቷል።

ይህ የቦንድ ሽያጭ ፕሬዚዳንት ማሃማ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ንቅናቄ ለመፍጠር እና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማነቃቃት የቀረጹት የ "ቢግ ፑሽ" ተነሳሽነት አካል እንደሆነ ተነግሯል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0