ኢትዮጵያ በ2019 ወደ ህዋ የምትልከው ሦስተኛ ሳተላይት የአምስት ዓመት አገልግሎት ይኖረዋል - የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በ2019 ወደ ህዋ የምትልከው ሦስተኛ ሳተላይት የአምስት ዓመት አገልግሎት ይኖረዋል - የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት
ኢትዮጵያ በ2019 ወደ ህዋ የምትልከው ሦስተኛ ሳተላይት የአምስት ዓመት አገልግሎት ይኖረዋል - የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.01.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በ2019 ወደ ህዋ የምትልከው ሦስተኛ ሳተላይት የአምስት ዓመት አገልግሎት ይኖረዋል - የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት

ET-RSS2 የተሰኘው አዲሱ ሳተላይት ጥራት ያለው ምስል የማንሳት አቅም፣ ረዥም የአገልግሎት ዘመን እና ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ መረጃዎችን ተደራሽ የሚያደርግ እንደሚሆን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ ተናግረዋል፡፡

ይህም ሀገሪቱ በህዋ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላትን ራዕይ ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በሳተላይት ተልዕኮዎች አማካኝነት የመረጃ መቀበያ፣ ትንተና እና አስተዳደር ላይ ተቋማዊ አቅሟን ከማሳደጓም በላይ ያላትን ተግባራዊ ተሞክሮ እያሻሻለች መሆኑን እንደሚያሳይ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የተላኩት ሳተላይቶች በምግብ ዋስትና፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር፣ በከተማ ፕላን እና በብሔራዊ ደህንነት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መረጃዎችን ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ኢንቲትዩቱ ጠቁሟል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም፤ ET-RSS1 እና ET-SMART-RSS የተሰኙ ሁለት የመሬት ምልከታ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ መላኳ ይታወሳል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0