የየመን ተገንጣይ መሪ በግዛቷ አቋርጦ ስለማምለጡ እየመረመረች መሆኑን ሶማሊያ አስታወቀች
16:16 09.01.2026 (የተሻሻለ: 16:24 09.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የየመን ተገንጣይ መሪ በግዛቷ አቋርጦ ስለማምለጡ እየመረመረች መሆኑን ሶማሊያ አስታወቀች
የየመን ተገንጣይ የደቡብ ሽግግር ምክር ቤት መሪ አይዳሩስ አል-ዙበይዲ፤ በሶማሊያ የአየር ክልል አድርጎ ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ማምለጡን የሚገልጹ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ፤ መንግሥት ከሌሎች አጋሮች ጋር በመሆን የሕግ ጥሰት ስለመፈፀሙ እያጣራ መሆኑን የሀገሪቱ የኢሚግሬሽን ኤጀንሲ አስታውቋል።
በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው የየመን አረብ ጥምረት፤ አል-ዙበይዲ በዩኤኢ መኮንኖች እርዳታ ማምለጣቸውን ቀደም ብሎ አስታውቆ ነበር። ይህ የሆነው የደቡብ ሽግግር ምክር ቤት መሪ፤ ወታደሮቻቸው ምስራቃዊ ግዛቶችን እንዲቆጣጠሩ ካዘዙ እና በተናጠል "ደቡብ አረቢያ" የተባለ ነፃ መንግሥት መመስረታቸውን ካወጁ በኋላ ነው።
በሶማሊያ ግዛት ውስጥ የሚደረግ ማንኛውም ያልተፈቀደ ኦፕሬሽን የሀገሪቱን ሉዓላዊነት በእጅጉ የሚጥስ መሆኑን መንግሥት አጽንዖት ሰጥቷል።
በተጨማሪም ሶማሊያ የየመንን ግጭት ለመፍታት በሪያድ የሚካሄደው ውይይት ትክክለኛው የፖለቲካ ሂደት ነው የሚለውን የሳዑዲ አረቢያ ጥሪ እንደምትደግፍ በድጋሚ አረጋግጣለች። አል-ዙበይዲ ከዚህ የሰላም ሂደት መሸሻቸው ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን እንደሚያደናቅፍ የሶማሊያ መንግሥት አስጠንቅቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X