ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ከ704 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቧን አስታወቀች

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ከ704 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቧን አስታወቀች
ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ከ704 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቧን አስታወቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.01.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ከ704 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቧን አስታወቀች

በግማሽ ዓመቱ ከተሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ ውስጥ 362.4 ቢሊዮን ብሩ ከሀገር ውስጥ ታክስ፤ ቀሪው 341.9 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ እንደተሰበሰበ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ63.7 ቢሊዮን ብር አብላጫ እንዳለውም ተጠቁሟል፡፡

ይህ አፈጻጸም ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛውን የገቢ ግኝት ያስመዘገበችበት መሆኑን አገልግሎቱ በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ የኢኮኖሚ ማሻሽያዎች ለተገኝው ውጤት መነሻ መሆናቸውን ተቋሙ በመግለጫው አመላክቷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0