የኤኤንሲ 114ኛ ዓመት - የመታደስ፣ የመገምገም እና ለደቡብ አፍሪካ ሕዝብ የገባውን ቃል ዳግም የማረጋገጥ መሆኑን ፓርቲው ገልጿል
የኤኤንሲ 114ኛ ዓመት - የመታደስ፣ የመገምገም እና ለደቡብ አፍሪካ ሕዝብ የገባውን ቃል ዳግም የማረጋገጥ መሆኑን ፓርቲው ገልጿል
“የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) የተገነባው ለምቾት ሳይሆን ለትግል ነው፤ ለአገልግሎት እንጂ ለሥልጣን ሆኖ አያውቅም። ከፊታችን የሚጠብቀን መንገድ ድፍረት፣ ሐቀኝነት እና የጋራ ጥረት ይጠይቃል” ሲል የደቡብ አፍሪካ ፓርቲ ዛሬ 114ኛ ዓመቱን ሲያከብር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የአፍሪካ አንጋፋው የነጻነት ንቅናቄ የሆነው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ይህን ምዕራፍ በትህትና እና በቆራጥነት ተቀብሎ የሚከተለውን ገልጿል፦
▪ መታደስ መፈክር ሳይሆን ተግባር ነው፤ ሥነምግባር ያለው አመራር፣ ድርጅታዊ ምግባር እና ለዜጎች የተሻለ የዕለት ተዕለት ኑሮ ይጠይቃል።
▪ የውስጥ ማንሰራራት በጠንካራ ተጠያቂነት፣ በካድሬዎች መታደስ እና ከማኅበረሰቦች ጋር በቃል ሳይሆን በተግባር ዳግም መገናኘት አለበት።
▪ ፓርቲው ደቡብ አፍሪካውያንን ዘር፣ መደብ፣ ፆታ እና ትውልድ ሳይለይ የማዋሃድ ብቸኛው ንቅናቄ ነው።
▪ ለብሔራዊ ሉዓላዊነት እና ለሰላማዊ ባለብዙ ወገን ዓለም አቀፍ ሥርዓት ይቆማል፡፡ እየጨመረ በመጣው ውጥረት ውስጥ ዓለም አቀፍ ትብብርን ይጠይቃል።
▪ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የኤኤንሲን የ2026 ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ያደርጋሉ።
የኤኤንሲን 114ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ራማፎሳ የተገኙበትን አከባበር ድባብ በስፑትኒክ አፍሪካ የቪዲዮ ቅንብር ይመልከቱ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X