የአሜሪካ ሴኔት በቬንዙዌላ ላይ የጦር ኃይል መጠቀምን የሚከለክል ውሳኔ አሳለፈ
20:18 08.01.2026 (የተሻሻለ: 20:24 08.01.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ሴኔት በቬንዙዌላ ላይ የጦር ኃይል መጠቀምን የሚከለክል ውሳኔ አሳለፈ
ዛሬ ሐሙስ በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት 52 ሴናተሮች ውሳኔውን ሲደግፉ፣ 47ቱ ተቃውመውታል።
የስብሰባው ሰብሳቢ "የውሳኔ ሐሳቡ ፀድቋል" ብለዋል።
በጥር 3 ቀን 2026 ፣ አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ ዐቢይ ዘመቻ በማካሄድ ፕሬዝዳንት ማዱሮን እና ባለቤታቸውን በመያዝ ወደ ኒውዮርክ ወስዳቸዋለች፡፡ ትራምፕ "የአደንዛዥ ዕፅ ሽብርተኝነት" ፈጽመዋል ሲሉ ከሠስሰዋቸዋል። ካራካስ የተባበሩት መንግሥታት የአስቸኳይ ስብሰባን ጠርታለች፤ የቬንዙዌላ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደሞ ታሕሣሥ 5 ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ለፈጸሙት ምክትል ፕሬዝዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ የፕሬዝዳንታዊ ኃላፊነትን አስተላልፏል፡፡
ሩሲያ እና ሌሎች በርካታ አገራት የአሜሪካን ድርጊት በብርቱ በማውገዝ፣ የማዱሮን መፈታት በመጠየቅ ተጨማሪ ውጥረትን አንዳይቀጥልም አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X