ኢትዮጵያ እና ቻይና በብዝኃ ትብብር መስኮች አጋርነታቸውን ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነተ ገለፁ
19:55 08.01.2026 (የተሻሻለ: 20:04 08.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ቻይና በብዝኃ ትብብር መስኮች አጋርነታቸውን ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነተ ገለፁ
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቴዎስ ከቻይና አቻቸው ዋንግ ዪ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ላላት ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ ገልጸዋል።
ሚኒስትር ጌድዮን ኢትዮጵያ በቤልት ኤንድ ሮድ፣ በብሪክስ ፕላስ እና በቻይና-አፍሪካ የትብብር ፎረም ያላትን አጋርነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። ቻይና በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ልማት ዙሪያ ያቀረበችውን ተነሳሽነትም አድንቀዋል።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በበኩላቸው፣ የ2026 የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ መጀመራቸው ቻይና ለሀገሪቱ ያላትን ታማኝ አጋርነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው፤ ትብብሩን ለማጠናከር ቃል ገብተዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ የትብብር መድረኮች ላይ ያላቸውን ስትራቴጂካዊ ቅንጅት ለማጠናከር መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/