https://amh.sputniknews.africa/20260108/2828058.html
አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ የምታደርገው ቁጥጥር ከአንድ ዓመት ተሻግሮ "ለረዥም ግዜያት" ሊቀጥል ይችላል - ትራምፕ
አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ የምታደርገው ቁጥጥር ከአንድ ዓመት ተሻግሮ "ለረዥም ግዜያት" ሊቀጥል ይችላል - ትራምፕ
Sputnik አፍሪካ
አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ የምታደርገው ቁጥጥር ከአንድ ዓመት ተሻግሮ "ለረዥም ግዜያት" ሊቀጥል ይችላል - ትራምፕ"ከአንድ ዓመት በጣም ለበለጠ ጊዜ" ሲሉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በነዳጅ የበለጸገችውን ቬንዙዌላን ለምን ያህል ጊዜ በቁጥጥሯ ስር... 08.01.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-01-08T19:25+0300
2026-01-08T19:25+0300
2026-01-08T19:34+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/01/08/2827904_0:0:800:450_1920x0_80_0_0_96c81b0350078d7fb02aeefff323d737.jpg
አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ የምታደርገው ቁጥጥር ከአንድ ዓመት ተሻግሮ "ለረዥም ግዜያት" ሊቀጥል ይችላል - ትራምፕ"ከአንድ ዓመት በጣም ለበለጠ ጊዜ" ሲሉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በነዳጅ የበለጸገችውን ቬንዙዌላን ለምን ያህል ጊዜ በቁጥጥሯ ስር እንደምታቆይ ከአንድ የአሜሪካ ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። በተጨማሪም ትራምፕ ወደፊት ሁኔታዎች "አስተማማኝ ሲሆኑ" ቬንዙዌላን የመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ ቁጥጥር እያደረገች የአገሪቱን ነዳጅ የመጠቀም፣ የነዳጅ ዋጋን የመቀነስ እና ለካራካስ ገንዘብ የመስጠት እቅድ እንዳላት ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።"አገሪቱን በጣም ትርፋማ በሆነ መንገድ እንደገና እንገነባታለን... ነዳጁን እንጠቀምበታለን፤ እንወስደዋለን። የነዳጅ ዋጋን እንዲቀንስ እናደርጋለን፤ እንዲሁም ቬንዙዌላ በከፍተኛ ሁኔታ ለሚያስፈልጋት እርዳታ ገንዘብ እንሰጣለን" ብለዋል። በተመሳሳይ፣ በካራካስ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ በመክፈት የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በጥር 3 ቀን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያደረጉት ትራምፕ፣ የአገሪቱን የነዳጅ ዘርፍ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል አምነዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/01/08/2827904_100:0:700:450_1920x0_80_0_0_ee1d548d14e1dae02600e07aae6adcbe.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ የምታደርገው ቁጥጥር ከአንድ ዓመት ተሻግሮ "ለረዥም ግዜያት" ሊቀጥል ይችላል - ትራምፕ
19:25 08.01.2026 (የተሻሻለ: 19:34 08.01.2026) አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ የምታደርገው ቁጥጥር ከአንድ ዓመት ተሻግሮ "ለረዥም ግዜያት" ሊቀጥል ይችላል - ትራምፕ
"ከአንድ ዓመት በጣም ለበለጠ ጊዜ" ሲሉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በነዳጅ የበለጸገችውን ቬንዙዌላን ለምን ያህል ጊዜ በቁጥጥሯ ስር እንደምታቆይ ከአንድ የአሜሪካ ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ትራምፕ ወደፊት ሁኔታዎች "አስተማማኝ ሲሆኑ" ቬንዙዌላን የመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።
አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ ቁጥጥር እያደረገች የአገሪቱን ነዳጅ የመጠቀም፣ የነዳጅ ዋጋን የመቀነስ እና ለካራካስ ገንዘብ የመስጠት እቅድ እንዳላት ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
"አገሪቱን በጣም ትርፋማ በሆነ መንገድ እንደገና እንገነባታለን... ነዳጁን እንጠቀምበታለን፤ እንወስደዋለን። የነዳጅ ዋጋን እንዲቀንስ እናደርጋለን፤ እንዲሁም ቬንዙዌላ በከፍተኛ ሁኔታ ለሚያስፈልጋት እርዳታ ገንዘብ እንሰጣለን" ብለዋል።
በተመሳሳይ፣ በካራካስ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ በመክፈት የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በጥር 3 ቀን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያደረጉት ትራምፕ፣ የአገሪቱን የነዳጅ ዘርፍ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል አምነዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X