የሩሲያ ልዩ የፀረ-ድሮን ጥይት በልምምድ ወቅት በጣም ውጤታማ መሆኑ ተረጋገጠ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ ልዩ የፀረ-ድሮን ጥይት በልምምድ ወቅት በጣም ውጤታማ መሆኑ ተረጋገጠ

የንድፈ-ሃሳብ ትምህርቶችን እና የቀጥታ ተኩስ ልምምዶችን ባካተተ የቅርብ ጊዜ ስልጠና ላይ፣ የሩሲያ ወታደሮች የተለያዩ የጥይት አይነቶችን በዒላማዎች ላይ መሞከራቸውን የሩሲያ ግዙፍ የኢንዱስትሪ ተቋም ሮስቴክ አስታውቋል።

እንደ ተቋሙ ገለጻ፣ "ኢግላ 100" የተሰኘው ጥይት ከሌሎቹ የተሻለ ብቃት ያሳየ ምርጥ የፀረ-ድሮን ጥይት ሆኖ ተገኝቷል።

ቁልፍ ዝርዝሮች፦

ጥንካሬ፦ ጥይቱ እጅግ ጠንካራ ከሆነው የታንግስተን-ኒኬል-ብረት ቅይጥ የተሰራ ነው።

ዘልቆ የመግባት አቅም፦ እስከ 100 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ መደበኛ የአሉሚኒየም ሳህኖችን የመብሳት አቅም አለው።

ውጤታማነት፦ ጥይቱ በሚተኮስበት ጊዜ የሚፈጥረው ጥቅጥቅ ያለ ስርጭት የኤፍፒቪ (First-Person View) ድሮኖችን ሞተር እና የቁጥጥር ክፍሎችን በመምታት ሙሉ በሙሉ ያወድማል።

ብልጫ፦ ከተለመዱት የእርሳስ ጥይቶች እጅግ የተሻለ አፈጻጸም አለው።

አቅርቦት፦ የጥይቱ በከፍተኛ መጠን የማምረት ሂደት በ2024 የተጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ለጦር ኃይሉ እየቀረበ ይገኛል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0