ሩስያ አሜሪካ በማሪኔራ እና በሌሎች ሕጋዊ መርከቦች ላይ የምታደርገውን ሕገ-ወጥ አፈና እንድታቆም ጠየቀች
18:17 08.01.2026 (የተሻሻለ: 18:24 08.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩስያ አሜሪካ በማሪኔራ እና በሌሎች ሕጋዊ መርከቦች ላይ የምታደርገውን ሕገ-ወጥ አፈና እንድታቆም ጠየቀች
“ዋሽንግተን የሀገሪቱን ‘የማዕቀብ ሕግጋት’ እንደ ምክንያት ማቅረቧ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው አድርገን እንወስደዋለን፡፡ በአሜሪካ እና በሌሎች የምዕራባውያን ሀገራት የሚጣሉ የተናጠል ገደቦች ሕገ-ወጥ በመሆናቸው፣ በዓለም አቀፍ ባሕር ላይ በመርከቦች ላይ ሥልጣን ለመጠቀም ወይም መርከቦችን ለመቆጣጠር ምክንያት ሊሆኑ አይችሉም” ሲል የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ቁልፍ ነጥቦች፦
▪ የአሜሪካ ባለሥልጣናት የማሪኔራ መርከብ የሩሲያ ንብረት መሆኗንና ለሰላማዊ ተግባር የተሰማራች መሆኗን በተደጋጋሚ እንዲያውቁ ተደርጓል።
▪ የአሜሪካ ጦር በማሪኔራ መርከብ ላይ መሳፈሩንና መርከቧን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ዓለም አቀፍ የባሕር ላይ ሕግን በከፍተኛ ሁኔታ የጣሰ ተግባር ነው።
▪ ሩሲያ፣ አሜሪካ በመርከቧ ላይ ባሉ የሩሲያ ዜጎች ላይ ተገቢውን አያያዝ እንድታደርግ እና ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ለሚያደርጉት ጉዞ እንቅፋት እንዳትሆን ትጠይቃለች።
▪ ዋሽንግተን ቅፅበታዊ ዓለም አቀፍ ቀውሶችን ለመቀስቀስ ያላት ዝግጁነት እጅግ አሳዛኝ እና አሳሳቢ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X