የቻይና እና የአፍሪካ ግንኙነት በእርስ በእርስ መከባበር ላይ የተመሠረተ ነው- ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ
17:44 08.01.2026 (የተሻሻለ: 18:04 08.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቻይና እና የአፍሪካ ግንኙነት በእርስ በእርስ መከባበር ላይ የተመሠረተ ነው- ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ
በ2026 የቻይና አፍሪካ የህዝብ ለህዝብ ልውውጥ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እንዳሉት የቻይና አፍሪካ ትብብር በተለይም በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በአቅም ግንባታ ዘርፎች አመርቂ ውጤቶች እያስገኘ ነው።
የ"ቤልት ኤንድ ሮድ" ተነሳሽነት እና የቻይና አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ፎረም ለግንኙነቱ ማደግ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ "የቴክኖሎጂ አብዮትና እድገት ለአፍሪካውያን መነሳሳትን ፈጥሯል።" ማለታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ እና በአረንጓዴ ኃይል ልማቶች ከቻይና ጋር ግንኙነቷን ማጠናከር እንደምትፈልግ ታዬ አፅ ቀ ሥላሴ ተናግረዋል። በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በትምህርት ልማት መስኮች ከቻይና ጋር የሚደረገው ትብብር ለቀጣይ የአገሪቱ ዘላቂ ልማት ወሳኝ መሆኑንም አስረድተዋል።
የህዝብ ለህዝብ ልውውጥ መድረኩ በቻይና እና የአፍሪካ ሃገራት መካከል ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን ለማሳለጥ፣ ማኅበራዊ ግንኙነትን ለማሳደግ እና የባህል ትስስርን ለማጠናከር አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ አክለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X