የቻይና–አፍሪካ ልውውጦች ወዳጅነትን፣ የወጣቶችን ተሳትፎን እና ዓለም አቀፍ ሰላምን ያጠናክራሉ – ዋንግ ዪ

ሰብስክራይብ

የቻይና–አፍሪካ ልውውጦች ወዳጅነትን፣ የወጣቶችን ተሳትፎን እና ዓለም አቀፍ ሰላምን ያጠናክራሉ – ዋንግ ዪ

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የቻይና አፍሪካ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት ሃገራቸው ከአፍሪካ ሃገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመረችበትን 70ኛ ዓመት በምታከብርበት በዚህ ወቅት ከመሪዎች ጋር ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

“የቻይና-አፍሪካ ወዳጅነት በዚህ አዲስ ታሪካዊ መነሻ ነጥብ በሕዝቦቻችን መካከል ጥልቅ ሥር እንዲሰድ ለመርዳት አስፈላጊ ነው። በሥልጣኔዎች መካከል የሚደረግ ልውውጥ እና የጋራ ትምህርት ለሰው ልጅ ሥልጣኔ እንዲሁም ለዓለም ሰላምና ልማት ቀጣይነት ያለው ግፊት ይሰጣል።” ብለዋል።

ዋንግ ዪ በቻይና እና አፍሪካ ሥልጣኔዎች መካከል የሚደረግ የልምድ ልውውጥ እና የጋራ የትምህርት ትብብር ለዓለም ሰላምና ልማት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ከ2.8 ቢሊዮን በላይ በሆኑ የቻይና እና የአፍሪካ ሕዝቦች መካከል የተፈጠረው ጠንካራ ትስስር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም የደቡብ ለደቡብ ትብብርን ለማጠናከር ለሚደረጉ የጋራ ጥረቶች አዳዲስ አስተዋፅዖዎችን እንደሚያደርግ መግለጻቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየቻይና–አፍሪካ ልውውጦች ወዳጅነትን፣ የወጣቶችን ተሳትፎን እና ዓለም አቀፍ ሰላምን ያጠናክራሉ – ዋንግ ዪ
የቻይና–አፍሪካ ልውውጦች ወዳጅነትን፣ የወጣቶችን ተሳትፎን እና ዓለም አቀፍ ሰላምን ያጠናክራሉ – ዋንግ ዪ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.01.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0