ኢትዮጵያ 14 አትሌቶቿ የአሜሪካ ቪዛ በመከልከላቸው ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የታዳጊዎች ውድድር ውጪ መሆኗ ተገለፀ
16:46 08.01.2026 (የተሻሻለ: 16:54 08.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ 14 አትሌቶቿ የአሜሪካ ቪዛ በመከልከላቸው ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የታዳጊዎች ውድድር ውጪ መሆኗ ተገለፀ
የቪዛ እገዳውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ልዑክ ቡድን በሁለቱም ፆታዎች በመጪው ቅዳሜ በታላሃሲ ከሚካሄደው የአገር አቋራጭ የረዥም ርቀት ውድድር ውጪ መሆኑን አዘጋጁ የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል፡፡
በውድድሩ ቢያንስ አራት አትሌቶች መሳተፍ ቢኖርባቸውም፤ ከ20 ዓመት በታች የተወዳዳሪዎች ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ በወንዶች አንድ አትሌት፣ በሴቶች ደግሞ ሶስት አትሌቶች ብቻ ማስመዝገቧ ተገልጿል፡፡
ይህም ኢትዮጵያ ከ1974 ጀምሮ በወንዶች፣ ከ1983 ጀምሮ ደግሞ በሴቶች በየዓመቱ ከ20 ዓመት በታች የቡድን ውድድር ሜዳሊያ የማግኘት ረጅም ታሪኳ እንዲያበቃ ያደርገዋል ሲል የዓለም አትሌቲክስ ጠቁሟል።
🪪 የአሜሪካ ኤምባሲ ቪዛውን የከለከለበት ግልጽ ምክንያት ያልተጠቀሰ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ደጋግሞ ጥያቄ ቢያቀርብም እንዳልተሳካለት ተገልጿል።
ውድድሩ በመጪው ቅዳሜ ጥር 2 በፍሎሪዳ ግዛት ታላሃሲ ከተማ በሚገኘው አፓላቺ ሪጅናል ፓርክ ይካሄዳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X