ተመድን ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት በማስቀረት እና የደቡባዊ ዓለምን ድምጽ በማጉላት ማሻሻል የአሜሪካን ድርጊቶች ለመቋቋም ወሳኝ ነው - የደቡብ አፍሪካ ፖለቲከኛ
20:59 07.01.2026 (የተሻሻለ: 21:04 07.01.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ተመድን ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት በማስቀረት እና የደቡባዊ ዓለምን ድምጽ በማጉላት ማሻሻል የአሜሪካን ድርጊቶች ለመቋቋም ወሳኝ ነው - የደቡብ አፍሪካ ፖለቲከኛ
"የተባበሩት መንግሥታት ከመሠረቱ እንደገና መዋቀር አለበት። ስለዚህ ልክ እንደ አሁኑ አስቸኳይ ጉዳዮች ላይ፣ ጠቅላላ ጉባዔው በአንድ ድምፅ አሜሪካን መቃወም አለበት" ሲሉ የአፍሪካ ማዪቡዬ ንቅናቄ ፕሬዝዳንት ፍሎይድ ሺቫምቡ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሺቫምቡ የአሜሪካ የቬንዙዌላውን ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን ጠልፎ መውሰድን በመጥቀስ፣ የአሁኑ የተመድ አወቃቀር ጊዜ ያለፈበት እና ኃያላን መንግሥታት በብቸኝነት እርምጃ እንዲወስዱ ያስችላል ሲሉ ሞግተዋል።
አስተያየት ሰጪው ተመድ ለምን "እንደገና መዋቀር" አለበት ብለው ያምናሉ?
▪ የ1945ቱ የተመድ ቻርተር ከዓለም አቀፍ እውነታዎች ጋር አይሄድም፤ በተለይም አፍሪካ 54 አባል ሀገራት እና 1.4 ቢሊዮን ሕዝብ ቢኖራትም በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር የላትም።
▪ሺቫምቡ ድምፅን በድምፅ የመሻር (ቬቶ) መብትን አንድ ሀገር ዓለም አቀፋዊ ስምምነትን እንዲሽር የሚያስችል ጉድለት ነው በማለት ኮንነዋል። ይህ በኩባ እና ፍልስጤም ጉዳዮች ላይ እንደታየው አንድም ሀገር እንዲህ ያለ ሥልጣን ሊኖረው እንደማይገባ አጥብቀው ተናግረዋል።
▪ወደፊት የሚመጣው አካሄድ፤ የተባበሩት ደቡባዊ ዓለም የተጨቆኑ ድምጾችን የሚያሰማ እና በቬንዙዌላ የቅርብ ጊዜ ውጥረት መጨመርን የመሳሰሉ ግጭቶችን መከላከል የሚችል የተሻሻለ የተባበሩት መንግሥታትን ለመፍጠር መጣር ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X