በቡርኪና ፋሶ የመፈንቅለ መንግሥት ሴራ ከሸፈ - የቀድሞው መሪ ዳሚባ ዋና አቀናባሪ መሆናቸው ተገለጸ - ሚኒስትሩ

በቡርኪና ፋሶ የመፈንቅለ መንግሥት ሴራ ከሸፈ - የቀድሞው መሪ ዳሚባ ዋና አቀናባሪ መሆናቸው ተገለጸ - ሚኒስትሩ
የቡርኪና ፋሶ የደህንነት ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና በቴሌቪዥን በተላለፈ ቪዲዮ መልዕክት ላይ የሚከተሉትን ዝርዝሮች አጋርተዋል፡-
▪ በታኅሣሥ 25 "ሀገሪቱን የማተራመስ ሙከራው" ታቅዶ ነበር።
▪ አቀናባሪዎቹ ኢብራሂም ትራውሬን እና በርካታ ወታደራዊና ሲቪል ባለሥልጣናትን ለመግደል፣ "የድሮን ጣቢያን" ከጥቅም ውጪ ለማድረግ እና በመቀጠልም "በውጭ ኃይሎች የሚደረግ የመሬት ላይ ወታደራዊ ጣልቃገብነት" ለማድረግ አስበው ነበር።
▪ "ዋናው ተዋናይ" እ.ኤ.አ.በመስከረም 30, 2022 በኢብራሂም ትራኦሬ ከሥልጣን የተወገዱት እና በአሁኑ ጊዜ በቶጎ በግዞት የሚገኙት የቀድሞ የሽግግር ፕሬዝዳንት ፖል-ሄንሪ ሳንዳኦጎ ዳሚባ ናቸው።
▪ "አብዛኛው የገንዘብ ድጋፍ የመጣው ከኮት ዲቯር ሲሆን፣ የቅርቡ አስተዋፅዖ 70 ሚሊዮን እንደደረሰ ተዘግቧል።"
▪ ምርመራ እና አሰሳ እየተካሄደ ሲሆን በርካታ ሲቪሎችም ታስረዋል። ሁኔታው በአሁኑ ጊዜ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ሁሉም ተሳታፊዎች "በፋሶ ዓቃቤ ሕግ ፊት ይቀርባሉ። የሕግ የበላይነትም ሙሉ በሙሉ ይተገበራል።"
ሚኒስትሩ "በምርመራ ላይ ያሉ ቁልፍ ግለሰቦች የእምነት ቃላቸውን የሚገልጹ ቪዲዮዎችን" ለመገናኛ ብዙኃን እንደሚለቁ ቃል ገብተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X