ዐቢይ አሕመድ በቤተሰብ ደረጃ ለ150 ዜጎች የተዘጋጀውን የቱሉ አራራ የተቀናጀ ሞዴል መንደርን በይፋ መረቁ
13:21 07.01.2026 (የተሻሻለ: 13:34 07.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዐቢይ አሕመድ በቤተሰብ ደረጃ ለ150 ዜጎች የተዘጋጀውን የቱሉ አራራ የተቀናጀ ሞዴል መንደርን በይፋ መረቁ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ጋር በመሆን፣ የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ ግብርን ወደ ላቀ ከፍታ ያሸጋገረውን የቱሉ አራራ የተቀናጀ ሞዴል መንደርን መመረቃቸውን አስታውቀዋል፡፡
ዐቢይ አሕመድ እንደገለጹት ይህ ሞዴል መንደር፦
በ7 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ነው፡፡
እያንዳንዱ ቤት 2 መኝታ ክፍሎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 5 ክፍሎች አሉት፡፡
የውስጥ ለውስጥ መንገድ ተሰርቶለታል፡፡
የኤሌክትሪክና የሶላር ኃይል ተዘርግቶለታል፡፡
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስፍራ እና
የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ያካተተ ነው።
“የልማት ሥራ የወተት ላሞች እና የዶሮ እርባታን እንዲሁም የጓሮ አትክልት ልማትን አጣምሮ የያዘ ሲሆን፣ እስከ መገበያያ ስፍራ የሚደርስ የተቀናጀ የንግድ ሰንሰለት ተፈጥሮለታል።” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X








