የወደፊት አፍሪካውያን ካህናት በሩሲያ የቅድመ-ልደት መንፈሳዊ ጉዞ አደረጉ - የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
12:39 07.01.2026 (የተሻሻለ: 12:44 07.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የወደፊት አፍሪካውያን ካህናት በሩሲያ የቅድመ-ልደት መንፈሳዊ ጉዞ አደረጉ - የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአፍሪካ ፓትርያርካዊ ሀገረ ስብከት እንዳስታወቀው፤ የገና ጾምን ምክንያት በማድረግ በሩሲያ ቲዎሎጂካል ሰሚናሪ የሚማሩ የኬንያ እና የካሜሩን ተማሪዎች በፔንዛ ግዛት የሚገኘውን የቅዱስ ሰርግዮስ ዘራዶኔዝ ቤተክርስቲያንን ጎብኝተዋል።
ተማሪዎቹ የቤተክርስቲያኑን ቅጥር ግቢ የጎበኙ ሲሆን፤ በቅድስናቸው፣ በምናኔ ሕይወታቸውና ከዕረፍታቸው በኋላ በሚፈጸሙ ተአምራት ለሚታወቁት የ19ኛው ክፍለ ዘመን ሩሲያዊ ጻድቅ የኦሌኔቮው ዮሐንስ ንዋያተ ቅድሳትም የአክብሮት ሰላምታ ማቅረባቸውን ሀገረ ስብከቱ ገልጿል።
የኦርቶዶክስ የገና በዓል ከ40 ቀናት የጾመ ገና ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት የሚያዘክር ሲሆን በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ደማቅ በዓላት ውስጥ አንዱ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


