‘ሰላም’ ያለ ምንም ዓይነት እርምጃ? — ደቡብ አፍሪካዊ የሶሻሊስት አክቲቪስት የብሪቲሽ ካውንስልን ግብዝነት አጋለጠች

ሰብስክራይብ

ሰላም’ ያለ ምንም ዓይነት እርምጃ? — ደቡብ አፍሪካዊ የሶሻሊስት አክቲቪስት የብሪቲሽ ካውንስልን ግብዝነት አጋለጠች

የብሪቲሽ ካውንስል “ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን በማጠናከር ሰላምን እንደሚያበረታታ” ቢናገርም፤ ለዘር ማጥፋት ዘመቻ የሚያደርገውን ድጋፍ ለማቆም ወይም በረሃብ ለተጎዱ ተቃዋሚዎች የህክምና እርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለም ስትል የሠራተኞች እና የሶሻሊስት ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ጁላይ ኤክለስ ገልጻለች።

አሁን በብሪቲሽ እስር ቤት ከ60 ቀናት በላይ የረሃብ አድማ ላይ የቆዩትን የፍልስጤም አክሽን አክቲቪስቶች ለመደገፍ በተሰባሰቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች ተጠያቂ ሲደረግ፤ “ምንም የማድረግ አቅም እንደሌለው” ምላሽ ይሠጣል ስትል ለስፑትኒክ አፍሪካ ከተቃውሞ ሰልፉ ጎን ለጎን ተናግራለች።

ማክሰኞ በጆሃንስበርግ በሚገኘው የብሪቲሽ ካውንል ደጃፍ በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ፤ ተቃዋሚዎች የእንግሊዝ-እስራኤል ወታደራዊ ትብብርን በመቃወም የታሰሩ የፍልስጤም ደጋፊ አክቲቪስቶች እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0