የቬንዙዌላ ቀውስ የደቡባዊ ዓለም አንድነት አጣዳፊ እንደሆነ አሳይቷል - ኢትዮጵያዊ ምሁር
19:38 06.01.2026 (የተሻሻለ: 20:24 06.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቬንዙዌላ ቀውስ የደቡባዊ ዓለም አንድነት አጣዳፊ እንደሆነ አሳይቷል - ኢትዮጵያዊ ምሁር
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር አስናቀ ከፋለ፤ አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ የወሰደችው እርምጃ በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ እና በእስያ የሚገኙ ሀገራት አንድ ግንባር በመፍጠር ሉዓላዊነታቸውን እንዲከላከሉ ሊገፋፋ ይገባል ብለዋል።
ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኩባ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ቀጣይዋ ዒላማ ልትሆን ትችላለች የሚለውን አስተሳሰብ ውድቅ በማድረግ፤ የሃቫናን ጠንካራ የመረጃና ወታደራዊ ዝግጅት ጠቅሰዋል።
"ኩባውያን ሲአይኤን 'ቤይ ኦፍ ፒግስ' ላይ ድል አድርገዋል። አሜሪካውያን ሃቫና ላይ ተመሳሳይ ዘመቻ የሚሞክሩ አይመስለኝም" ብለዋል።
ምሁሩ በተጨማሪም ኃያላን መንግሥታት ጣልቃ ሲገቡ ሉዓላዊ መንግሥታትን በመጠበቅ ረገድ ተመድ ያለበትን መዋቅራዊ ድክመት ተችተዋል።
"ተመድ የኢራቅን ወረራ ወይም የጋዛን ግፍ ማስቆም አልቻለም። የፀጥታው ምክር ቤት መብቶችን በሚጥሱ መንግሥታት ላይ ቆራጥ እርምጃ መውሰድ አለመቻሉ ድርጅቱ ደካማ የሆኑ ሀገራትን ለመከላከል ያለውን ውስን አቅም ያሳያል" ሲሉም ሞግተዋል።
የደቡባዊ ዓለም "የውጭ የበላይነትን ለመጋፈጥ እና የፖለቲካ ነጻነትን ለመጠበቅ" ብቸኛው አዋጭ መንገድ አንድነት ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X