የአእላፋት ዝማሬ መርኃ-ግብር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተካሄደ
19:24 06.01.2026 (የተሻሻለ: 20:14 06.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአእላፋት ዝማሬ መርኃ-ግብር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተካሄደ
የአእላፋት ዝማሬ በኢትዮጵያ የገና በዓል ዋዜማ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ምዕመናን የሚገኙበት ትልቅ መርኃ-ግብር ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄርያቆስ እና በርካታ የቤተክርስቲያኒቱ የኃይማኖት መሪዎች ዓለም አቀፍ እውቅናን እያገኘ በሚገኘው በዚህ ዝግጅት ላይ መገኘታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ከቦታው ዘግቧል።
በአንድ ጊዜ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ዘማሪዎችን የሚያሣትፈው የአእላፋት ዝማሬ ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ ሲካሄድ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/ 


