አሜሪካ የቬንዙዌላ ፕሬዚዳንትን መያዝ ዓለም አቀፍ መረጋጋትን ያናጋል - የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

አሜሪካ የቬንዙዌላ ፕሬዚዳንትን መያዝ ዓለም አቀፍ መረጋጋትን ያናጋል - የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

“አሜሪካ የቬንዙዌላ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እንደ ሀገር መሪ ያላቸውን ደረጃ ችላ በማለት በራሷ ፍርድ ቤት ክስ መክፈቷ የቬንዙዌላን ሉዓላዊነት በከፍተኛ ሁኔታ በመጣስ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን መረጋጋት አናግቷል። የትኛውም ሀገር የራሱን ሕግ ከዓለም አቀፍ ሕግ በላይ ሊያስቀምጥ አይችልም” ሲሉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ማኦ በመግለጫቸው ያነሷቸው ሌሎች ቁልፍ ሃሳቦች፦

◻ ቻይና፤ አሜሪካ የፕሬዚዳንት ማዱሮንና ባለቤታቸውን ሲሊያ ፍሎረስን የግል ደህንነት በማረጋገጥ በአስቸኳይ እንድትፈታ ጥሪ ታቀርባለች፡፡

◻ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ፤ በላቲን አሜሪካና በካሪቢያን ሰላምን ለማረጋገጥ ከክልላዊ አጋሮችና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ለመተባበር ዝግጁ ነው፡፡

◻ አሜሪካ ላይ ሊጣሉ ስለሚችሉ ማዕቀቦች በተመለከተ፤ ቻይና የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ ያለውን ሚና ትደግፋለች ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ማዱሮንና ባለቤታቸውን ባሳለፍነው ቅዳሜ በ “በዕፅ-ሽብርተኝነት” ክስ ስር በቁጥጥር ስር አውላ ወደ ኒው ዮርክ ማዛወሯ የሚታወስ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0