አሜሪካ ለቪዛ አመልካቾች እስከ 15 ሺህ ዶላር የገንዘብ ማስያዣ የምትጠይቅባቸውን ሀገራት ዝርዝር አሰፋች

አሜሪካ ለቪዛ አመልካቾች እስከ 15 ሺህ ዶላር የገንዘብ ማስያዣ የምትጠይቅባቸውን ሀገራት ዝርዝር አሰፋች
የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የቡታን፣ የቦትስዋና፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ የጊኒ፣ የጊኒ-ቢሳው፣ የናሚቢያ እና የቱርክሜኒስታን ዜጎችን ወደ አሜሪካ ለመግባት ማመልከት ከፈለጉ ከ5 ሺህ እስከ 15 ሺህ ዶላር የሚደርስ የገንዘብ ዋስትና (ቦንድ) ማስያዝ ካለባቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ አካቷል።
በይፋዊ የአሜሪካ መንግሥት ድረ-ገጽ ላይ በወጣው ማስታወቂያ መሠረት፤ ይህ አዲስ ደንብ ከታህሳስ 23 ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል።
የገንዘብ ዋስትና ማስያዣ ከተጣለባቸው ሀገራት አብዛኞቹ ከአፍሪካ አኅጉር ሲሆኑ ጠቅላላ ቁጥራቸው 13 ደርሷል። ከዚህ ቀደም ሞሪታኒያ፣ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ፣ ታንዛኒያ፣ ጋምቢያ፣ ማላዊ እና ዛምቢያ በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል።
የአሜሪካ አስተዳደር ፍልሰትን አስቸጋሪ ለማድረግ የወሰደው እርምጃ፤ ከዚህ በፊት ካስቀመጣቸው የአካል የቪዛ ቃለ መጠይቅ፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ታሪክ፣ የቀድሞ የጉዞ መረጃ እና የግልና የቤተሰብ የኑሮ ሁኔታዎችን የመግለጽ ነባር መስፈርቶች ላይ የሚታከል ነው።
የዋስትና ክፍያው ቪዛ ማግኘትን እንደማያረጋግጥ ሆኖም ቪዛው ከተከለከለ ወይም የቪዛው ባለቤት ሁሉንም መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ማክበሩ ከተረጋገጠ በኋላ ገንዘቡ ተመላሽ እንደሚደርግ የሚዲያ ዘገባዎች ገልጸዋል።
ቀደም ሲል ኒጀር፣ ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ በአሜሪካ ዜጎች ላይ የቪዛ እገዳ መጣላቸው ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X