ለኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚቀርበው የሀገር ውስጥ ግብዓት ከ5 በመቶ እንደማይበልጥ ተገለፀ
17:59 06.01.2026 (የተሻሻለ: 18:04 06.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ለኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚቀርበው የሀገር ውስጥ ግብዓት ከ5 በመቶ እንደማይበልጥ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ያካሄደው ጥናት እንዳረጋገጠው፤ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የተሠማሩ 95 በመቶ ፋብሪካዎች የሚጠቀሙት ግብዓት ከሀገር ውጭ የሚገባ ነው።
በዚህም ፓርኮቹ የውጭ ምንዛሬና ሀብት እንዳያመነጩ ዋነኛ እንቅፋት እንደሆነባቸው ጥናቱ ጠቁሟል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ጥናቱ ለችግሩ ያቀረባቸው ምክንያቶች፦
◻ ሀገር ውስጥ የሚመረቱ ጥሬ ዕቃዎች ጥራት ማነስ፣
◻ ምርቶቹን ወደ ፓርኮች በማጓጓዝ ረገድ የትራንስፖርትና የሎጀስቲክ ተግዳሮቶች፡፡
መንግሥት የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎች በጥራት እንዲመረቱ በማገዝ፣ ሎጀስቲኩን በማዘመን እንዲሁም የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃ የሚጠቀሙ ባለሀብቶችን በማበረታታት ጉድለቱን እንዲያሟላ ጥናቱ አመላክቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X