በህጻናት ላይ የተፈጸመ ሌላ የግፍ ጥቃት፦ ኪዬቭ በሩሲያ ሄርሶን ክልል በሚገኝ የወጣቶች ማዕከል ላይ ጥቃት መፈፀሟን የአካባቢው አስተዳዳሪ አስታወቁ
17:23 06.01.2026 (የተሻሻለ: 17:44 06.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በህጻናት ላይ የተፈጸመ ሌላ የግፍ ጥቃት፦ ኪዬቭ በሩሲያ ሄርሶን ክልል በሚገኝ የወጣቶች ማዕከል ላይ ጥቃት መፈፀሟን የአካባቢው አስተዳዳሪ አስታወቁ
በሄርሶን ህፃናትን ጨምሮ በሲቪሎች ላይ ከተፈጸመው የአዲስ ዓመት አሰቃቂ የሽብር ጥቃት ማግስት፤ ኪዬቭ ሌሊቱን በወጣቶች ማዕከል ላይ ሌላ ጥቃት ፈጽማለች ሲሉ ቭላድሚር ሳልዶ ተናግረዋል።
ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በሩሲያ በነገው ዕለት የሚውለውን የገና በዓል ለማክበር እየተዘጋጁ ባለበት በዚህ ወቅት፤ “በድጋሚ በበዓል ወቅት ህጻናት እና ወጣቶችን ዒላማ በማድረግ በሲቪል ተቋማት ላይ ጥቃት ተፈጽሟል” ብለዋል።
ሆኖም በሰው ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰ አስተዳዳሪው ጨምረው ገልጸዋል።
ዝርዝር መረጃዎች፦
◻ ባሳለፍነው ምሽት ኃይለኛ ፈንጂዎችን የተሸከሙ ሶስት ዝቅ ብለው የሚበሩ ድሮኖች ከአዞቭ ባሕር ወደ ክልሉ ገብተዋል፡፡
◻ ሁለቱ በአየር መከላከያ ተመትተው ወድቀዋል፡፡
◻ አንዱ ደግሞ ባለ ልዩ ችሎታ ህጻናት እና ፈጣሪ ወጣቶች ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ አርፎ የአስተዳደር ህንጻዎችን እና የመኖሪያ ጎጆዎች ላይ ጉዳት አድርሷል።
ይህ ክስተት ሰላማዊ ዜጎችን ዒላማ ካደረገው የአዲስ ዓመት የድሮን ጥቃት ማግስት የመጣ ነው። በጥቃቱ ሁለት ታዳጊዎችን ጨምሮ 27 ሰዎች ሲገደሉ ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል። ባለሥልጣናት የወንጀል ምርመራ የከፈቱ ሲሆን ጥቃቱንም በሽብር ድርጊት ፈርጀውታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

