https://amh.sputniknews.africa
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በጊኒ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ተቀበለ፤ ማዕቀቦች እንዲነሱም ሐሳብ አቀርቧል
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በጊኒ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ተቀበለ፤ ማዕቀቦች እንዲነሱም ሐሳብ አቀርቧል
Sputnik አፍሪካ
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በጊኒ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ተቀበለ፤ ማዕቀቦች እንዲነሱም ሐሳብ አቀርቧልየአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ "የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ማሐሙድ አሊ ዩሱፍ፤ ለተመረጡት የጊኒ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ለተከበሩ ጄኔራል ማማዲ... 06.01.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-01-06T17:12+0300
2026-01-06T17:12+0300
2026-01-06T17:14+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/01/06/2798485_0:42:800:492_1920x0_80_0_0_1b39dc0e25b77abb29795e53f0c8792b.jpg
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በጊኒ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ተቀበለ፤ ማዕቀቦች እንዲነሱም ሐሳብ አቀርቧልየአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ "የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ማሐሙድ አሊ ዩሱፍ፤ ለተመረጡት የጊኒ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ለተከበሩ ጄኔራል ማማዲ ዱምቡያ ሞቅ ያለ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል" ብሏል። ሊቀምንበሩ፤ ታኅሣሥ 19 የተካሄደውን ምርጫ "ሰላማዊና የተረጋጋ" እንዲሁም "ከዓለም አቀፍ መስፈርቶች እና ከሀገሪቱ የሕግ ማዕቀፍ ጋር በተጣጣመ መልኩ" የተከናወነ ሲሉ ገልጸውታል።መግለጫው አክሎም፤ "እ.ኤ.አ ከ2021 የሽግግር ግዜ ጀምሮ የጊኒ ሪፐብሊክ ያስመዘገበችውን መሻሻል ግምት ውስጥ በማስገባት፤ የአፍሪካ ኅብረት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሀገሪቱ ያለውን ሁኔታ በመገምገም በጊኒ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች የሚነሱበትን ሁኔታ እንዲያጤኑ ሊቀመንበሩ ያሳስባሉ" ብሏል። እ.ኤ.አ 2021 በመፈንቅለ መንግሥት ወደ ሥልጣን የመጡት ጄኔራል ዱምቡያ፤ በምርጫው 86.72 በመቶ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል። የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እሁድ ዕለት በይፋ ፕሬዚዳንትነታቸውን አውጇል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07ea/01/06/2798485_45:0:756:533_1920x0_80_0_0_f7261c0bfb7d964a313e0509daed592a.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በጊኒ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ተቀበለ፤ ማዕቀቦች እንዲነሱም ሐሳብ አቀርቧል
17:12 06.01.2026 (የተሻሻለ: 17:14 06.01.2026) የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በጊኒ የተካሄደውን ምርጫ ውጤት ተቀበለ፤ ማዕቀቦች እንዲነሱም ሐሳብ አቀርቧል
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ "የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ማሐሙድ አሊ ዩሱፍ፤ ለተመረጡት የጊኒ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ለተከበሩ ጄኔራል ማማዲ ዱምቡያ ሞቅ ያለ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል" ብሏል።
ሊቀምንበሩ፤ ታኅሣሥ 19 የተካሄደውን ምርጫ "ሰላማዊና የተረጋጋ" እንዲሁም "ከዓለም አቀፍ መስፈርቶች እና ከሀገሪቱ የሕግ ማዕቀፍ ጋር በተጣጣመ መልኩ" የተከናወነ ሲሉ ገልጸውታል።
መግለጫው አክሎም፤ "እ.ኤ.አ ከ2021 የሽግግር ግዜ ጀምሮ የጊኒ ሪፐብሊክ ያስመዘገበችውን መሻሻል ግምት ውስጥ በማስገባት፤ የአፍሪካ ኅብረት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሀገሪቱ ያለውን ሁኔታ በመገምገም በጊኒ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች የሚነሱበትን ሁኔታ እንዲያጤኑ ሊቀመንበሩ ያሳስባሉ" ብሏል።
እ.ኤ.አ 2021 በመፈንቅለ መንግሥት ወደ ሥልጣን የመጡት ጄኔራል ዱምቡያ፤ በምርጫው 86.72 በመቶ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል። የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እሁድ ዕለት በይፋ ፕሬዚዳንትነታቸውን አውጇል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X