በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ22 ሰዎች ሕይወት አለፈ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ22 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ22 ሰዎች ሕይወት አለፈ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.01.2026
ሰብስክራይብ

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ22 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አደጋው የተከሰተው ንጋት 11፡00 ሰዓት አካባቢ በሕገ-ወጥ ደላሎች ተታልለው ወደ ውጭ ሀገራት ለማቅናት የተሰባሰቡ ዜጎችን አጭቆ ሲጓዝ የነበረ ተሳቢ ተሽከርካሪ በሰመራ ከተማ አደባባይ ላይ በመገልበጡ እንደሆነ የአፋር ክልል የኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

በደረሰው አደጋ እስካሁን የ22 ሰዎች ሕይወት ማለፉ የተረጋገጠ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም ከጉዳቱ ስፋት አንጻር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

በአደጋው 30 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም 35 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ 65 ተጎጂዎች በዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የአፋር ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መሐመድ አሊ ቢኢዶ ተናግረዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ22 ሰዎች ሕይወት አለፈ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ22 ሰዎች ሕይወት አለፈ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0