ፎስቲን አርካንጅ ቱዋዴራ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸው ታወጀ

© telegram sputnik_ethiopiaፎስቲን አርካንጅ ቱዋዴራ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸው ታወጀ
ፎስቲን አርካንጅ ቱዋዴራ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸው ታወጀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.01.2026
ሰብስክራይብ

ፎስቲን አርካንጅ ቱዋዴራ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸው ታወጀ

ቱዋዴራ ታኅሣሥ 19 የተካሄደውን ምርጫ 76.15 በመቶ ድምፅ በማግኘት ለሦስተኛ ጊዜ እንደተመረጡ የሀገሪቱ ብሔራዊ የምርጫ ባለሥልጣን አስታውቋል።

◻ ዋና ተቀናቃኛቸው አኒሴ ጆርጅ ዶሎግሌ በ14.66 በመቶ ድምፅ ሁለተኛ ደረጃን ሲይዙ፤ ሄንሪ ማሪ ዶንድራ ደግሞ 3.19 በመቶ አግኝተዋል።

◻ በተመሳሳይ ቀን በተካሄዱት የፕሬዚዳንታዊ፣ የሕግ አውጪ፣ የክልላዊ እና ማዘጋጃ ቤት ምርጫዎች የመራጮች ተሳትፎ 52.43 በመቶ ነበር።

◻ የምርጫ ባለሥልጣኑ አኃዝ ጊዜያዊ ሲሆን የመጨረሻው ውጤት በጥር ወር መጨረሻ ላይ በሕገ-መንግሥታዊ ምክር ቤት ይፋ ይደረጋል።

ፎስቲን አርካንጅ ቱዋዴራ ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ በ2016፤ በ2020 ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ በድጋሚ ተመርጠዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0