አሜሪካ ቬንዙዌላ ላይ ያደረገችው ዘመቻ 'በግላጭ የታየ የአምባገነናዊነት አረመኔያዊ ማሳያ ነው' - አክቲቪስት
19:37 05.01.2026 (የተሻሻለ: 20:24 05.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አሜሪካ ቬንዙዌላ ላይ ያደረገችው ዘመቻ 'በግላጭ የታየ የአምባገነናዊነት አረመኔያዊ ማሳያ ነው' - አክቲቪስት
የደቡብ አፍሪካ የብረታ ብረት ሠራተኞች ብሔራዊ ማኅበር አባል ፋካሚሌ ህሉቢ-ማጆላ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገሩት፣ የአሜሪካ በቬንዙዌላ የምታካሂደው ጣልቃ ገብነት በዓለማችን ትልቁን የነዳጅ ክምችት ለመቆጣጠር ባላት ፍላጎት የተመራ ነው ብለዋል።
ማጆላ ሁሉም ተራማጅ እና ለዴሞክራሲ የቆሙ ኃይሎች የአሜሪካን ድርጊቶች ለማውገዝ እና ለቬንዙዌላ አጋርነታቸውን ለማሳየት አንድ መሆን አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል። ሁኔታውን ለማጋለጥ "የምግባር ድምጽ" እና "የምግባር መለኪያ" ሆነው መሥራት አለባቸው በለዋል።
ብሪክስ በተለይም ባለፉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት ባለው ሚና ምክንያት ጠንካራ አቋም መውሰድ አለበት ያሉት ህሉቢ-ማጆላ፣ ቡድኑ ወሳኝ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል ብለዋል።
በቬንዙዌላ ዙሪያ ያለውን ሁኔታ ለመፍታት ወታደራዊ ያልሆኑ መፍትሔዎች ተመራጭ መሆናቸውን ቢገልጹም፣ ግፊቶች ከጨመሩ ወታደራዊ ምላሾችን አለማግለል እንደማይገባ ማጆላ አስጠንቅቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X