ቬኔዝዌላ ውስጥ ያለው ቀውስ የደቡባዊ ዓለምን አንድነት አስፈላጊነትን ያሳያል — ባለሙያ
19:13 05.01.2026 (የተሻሻለ: 19:54 05.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቬኔዝዌላ ውስጥ ያለው ቀውስ የደቡባዊ ዓለምን አንድነት አስፈላጊነትን ያሳያል — ባለሙያ
አሜሪካ በቬኔዝዌላ ላይ የፈጸመችው ጣልቃ ገብነት ቀውስ የደቡባዊ ዓለምን ሀገራት አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩና ሉዓላዊነታቸውን እንዲከላከሉ ያለውን አስቸኳይ ፍላጎት የሚያጎላ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር አሰናቀ ከፋለ (ዶ/ር ) አስጠንቅቀዋል።
ባለሙያው ለስፑትኒክ አፍሪካ ሲናገሩ፣ ኩባ ወይም ሌሎች የላቲን አሜሪካ ሀገራት ቀጣይ ኢላማ ሊሆኑ ይችላሉ የሚለውን ግምት ውድቅ አድርገው፣ የሃቫናን ጠንካራ የስለላና ወታደራዊ አቅም ጠቅሰዋል።
“ኩባውያን ሲአይኤን ‘በባይ ኦፍ ፒግስ’ አሸንፈዋል። አሜሪካውያን ሃቫና ውስጥ ተመሳሳይ ዘመቻ ይሞክራሉ ብዬ አላስብም” ብለዋል።
ዶ/ር አስናቀ ‘ኃያላን’ በሌሎች ሀገራት የውጥ ጉዳይ ጣልቃ ሲገቡ የተባበሩት መንግሥታት፣ መንግሥታትን በመጠበቅ ረገድ ያለውን መዋቅራዊ ድክመትም አጉልቶ አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል።
“የተባበሩት መንግሥታት የኢራቅን ወረራ፣ እንዲሁም በጋዛ የተፈጸሙትን አስከፊ ድርጊቶች ማስቆም አልቻለም። የፀጥታው ምክር ቤት ድምጽን በድምጽ በመሻር መብት ባላቸው ሀገራት መንግሥታት ላይ ወሳኝ እርምጃ መውሰድ እንደማይችል ያመለክታል፤ ይህ ደግሞ ድርጅቱ ደካማ ሀገራትን ለመከላከል ያለውን አቅም ማነስ ያጋልጣል” ሲሉ አስረድተዋል።
የቬኔዝዌላ ቀውስ በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ እና በእስያ የሚገኙ ሀገራት ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ እና የተባበረ ድምጽ እንዲፈጥሩ እንደ አንድ የጋራ መነሳሻ ነጥብ ማገልገል እንዳለበት ባለሙያው ተናግረዋል።
“አንድነት የውጭ የበላይነትን ለመቋቋም እና የፖለቲካ ነፃነትን ለመጠበቅ ብቸኛው መንገድ ነው” ሲሉ ዶ/ር አስናቀ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X