ታሪክን በልኩ የመገምገም ልምድን ማዳበር ይገባል - አሉላ ፓንክረስት (ፕ/ር)
17:02 05.01.2026 (የተሻሻለ: 17:04 05.01.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ታሪክን በልኩ የመገምገም ልምድን ማዳበር ይገባል - አሉላ ፓንክረስት (ፕ/ር)
ማኅበራዊ አንትሮፖሎጂስቱ እና ተመራማሪ፣ ከወታደራዊው የደርግ መንግሥት ጀምሮ በቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ አሉታዊ የታሪክ ገጾች ላይ ብቻ የማተኮር ጠንካራ ልምምድ መኖሩን ይገልጻሉ።
"ንጉሰ ነገሥቱ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያን ነፃነት በማስጠበቅ እና አገሪቱን በማዘመን ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። የታሪክን አዎንታዊ እና አሉታዊ ገጽ መልሶ መገምገም አሁን ገና እየተጀመረ ያለ ነው።" ብለዋል።
አሉላ ፓንክረስት (ፕ/ር) ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ 'አያቴ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ' በሚል ርዕስ የተሰራው ዘጋቢ ፊልም ለዚህ የታሪክ መልሶ ግምገማ አስደናቂ አበርክቶ እንዳለውም አመላክተዋል።
“አያቴ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ” በሚል ርዕስ በንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሤ ሕይወት ላይ ያተኮረ ዘጋቢ ፊልም ቅዳሜ ታሕሣሥ 25፣ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ በቅቷል፡፡
ከዕሑድ ታሕሣሥ 25፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በነጻ ለሕዝብ እይታ ክፍት መሆኑንም የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X