አሜሪካ የቬንዙዌላን ነዳጅ መቆጣጠሯ አዲስ ዓለም አቀፍ የዋጋ ንረትን ሊያስከትል ይችላል – ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአሜሪካ የቬንዙዌላን ነዳጅ መቆጣጠሯ አዲስ ዓለም አቀፍ የዋጋ ንረትን ሊያስከትል ይችላል – ባለሙያ
አሜሪካ የቬንዙዌላን ነዳጅ መቆጣጠሯ አዲስ ዓለም አቀፍ የዋጋ ንረትን ሊያስከትል ይችላል – ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.01.2026
ሰብስክራይብ

  አሜሪካ የቬንዙዌላን ነዳጅ መቆጣጠሯ አዲስ ዓለም አቀፍ የዋጋ ንረትን ሊያስከትል ይችላል – ባለሙያ

በቬንዙዌላ የነዳጅ ምርት ሙሉ በሙሉ ከቆመ እና የአቅርቦት መስመሮች ከተቋረጡ፣ የነዳጅ ዋጋ በረጅም ጊዜ ውስጥ 100 ዶላር ሊደርስ ይችላል፤ ሲሉ  የሊቢያው ባለሙያ አብዱል ጀሊል ማዩፍ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡

በተለይም ይህች የደቡብ አሜሪካ ሀገር ከዓለም የነዳጅ ክምችት 19 በመቶ ያህሉን መያዟ ግምት ውስጥ ሲገባ፣ አሜሪካ የቬንዙዌላን ነዳጅ መቆጣጠሯ የወደፊቱን ዋጋ ሊነካ እንደሚችል አሳስበዋል፡፡

እንደ ባለሙያው ከሆነ ውጤቱ የሚወሰነው በቬንዙዌላ ቀውስ ባህሪ እና ቆይታ፣ እንዲሁም የቬንዙዌላ ህዝብ በአሜሪካ ለሚመራውና በሀገራቸው ላይ ለተከፈተው ጦርነት በሚሰጠው ምላሽ ላይ ነው።

በአጭር ጊዜ ውስጥ የኃይል ዋጋዎች በእጅጉ እንደሚጎዱ አጽንኦት የሰጡ ሲሆን፣ ይሁን እንጂ የበለጠ ከባድ መዘዞች ቀውሱ ምን ያህል በፍጥነት እንደሚጠናቀቅ ይወሰናል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0