ሩሲያን ጨምሮ የአምስት ሀገራት አየር ኃይሎች የሚሳተፉበት ትርኢት በቢሾፍቱ ሰማይ ስር ሊካሄድ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያን ጨምሮ የአምስት ሀገራት አየር ኃይሎች የሚሳተፉበት ትርኢት በቢሾፍቱ ሰማይ ስር ሊካሄድ ነው
ሩሲያን ጨምሮ የአምስት ሀገራት አየር ኃይሎች የሚሳተፉበት ትርኢት በቢሾፍቱ ሰማይ ስር ሊካሄድ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.01.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያን ጨምሮ የአምስት ሀገራት አየር ኃይሎች የሚሳተፉበት ትርኢት በቢሾፍቱ ሰማይ ስር ሊካሄድ ነው

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምሥረታ 90ኛ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ “የጥቁር አንበሳ የአየር ትርኢት 2026” ከጥር 15 እስከ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

እንደ ሚዲያው የሚሳተፉ ሀገራት፡-

የኢትዮጵያ፣

የሩሲያ፣

 የተባበሩት የአረብ ኤምሬቶች፣

የሞሮኮ እና

የቼክ ሪፐብሊክ አየር ኃይሎች ናቸው።

በተጨማሪ "የወደፊቱን የአቪዬሽን አቅም በጋራ እንገንባ" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ የቻይና፣ የሕንድ፣ የአሜሪካ እና የደቡብ አፍሪካ ግዙፍ ኩባንያዎች የሚካተቱበትና ከ25 ሀገራት በላይ የሚሳተፉበት የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2026 ይካሄዳል ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0