የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሦስት ዘመናዊ የቁም እንስሳት የግብይት ማዕከላትን በሦስት ክልሎች ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ
16:10 04.01.2026 (የተሻሻለ: 16:14 04.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሦስት ዘመናዊ የቁም እንስሳት የግብይት ማዕከላትን በሦስት ክልሎች ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ
በ220 ሚልዮን ብር ወጭ በኦሮሚያ ሞያሌ ቢቃ፣ በደቡብ ቀይ አፈር እና በደቡብ ምዕራብ ጀሙ ዘመናዊ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት የግብይት ማዕከላት ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ሚኒስቴሩ ከሦስት ድርጅቶች ጋር ተፈራርሟል።
በሶማሌ ደገሀቡር፣ በአፋር ሰመራ እና በኦሮሚያ ኤልብኮ በመገንባት ላይ የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት የግብይት ማዕከላት ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ሲል ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ የትስስር ገፁ አስነብቧል።
በ2017 ዓ.ም ከ630 ሺህ በላይ የቁም እንስሳት ወደ ኩዌት፣ ኦማን ሳዑዲ አረቢያ፣ ባህሬን የመን፣ ጅቡቲ እና ሶማሌ በመላክ ከዘርፉ ከ63 ሚልዮን ዶላር በላይ መገኘቱም ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X