የትራምፕ አዲሱ የሞንሮ ዶክትሪን ዓለም ምንም አይነት ደንቦች እንደሌሏት ያረጋግጣል - ዱጊን
14:23 04.01.2026 (የተሻሻለ: 14:24 04.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የትራምፕ አዲሱ የሞንሮ ዶክትሪን ዓለም ምንም አይነት ደንቦች እንደሌሏት ያረጋግጣል - ዱጊን
አሜሪካ በቬንዙዌላ ያከናወነችውን ወታደራዊ ዘመቻን ተከትሎ ፈላስፋው አሌክሳንደር ዱጊን እንደገለጹት፣ ድርጊቱ ከእንግዲህ ዓለም አቀፍ ሕግ አለመኖርዩን እና "ሁሉም ለራሱ የሚኖርበት ጊዜ መመጣቱን" ያረጋግጣል።
ሩሲያ በሌሎች የሚጫኑባትን ደንቦች ለማስቀረት የራሷን ተጽዕኖ ማረጋገጥ እንዳለባት በመሞገት፣ አገሪቱ የራሷን "ዩራሺያ የሞንሮ* ዶክትሪን" ሙሉ በሙሉ እንድትቀበል ጥሪ አቅርበዋል።
"ለሩሲያ የራሳችንን የሞንሮ ዶክትሪን መቀረጽ አለብን... እኔ በዚህ ላይ ከ30 ዓመታት በላይ ስሠራ ቆይቻለሁ" ሲሉ ዱጊን ገልጸዋል።
*የሞንሮ ዶክትሪን የአሜሪካ ምድር የራሷ የተፅዕኖ ክልል እንደሆነ እና አውሮፓውያኑ በቀጣናው ጣልቃ መግባት የሚከለክል የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጀምስ ሞንሮ የ1823 (እ.አ.አ. ) አዋጅ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X