የአልጄሪያ መንግሥት የፈረንሳይን የቅኝ ግዛት ታሪክ በወንጀል በመፈረጅ “ ትልቅ ብርታት አሳይቷል” - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአልጄሪያ መንግሥት የፈረንሳይን የቅኝ ግዛት ታሪክ በወንጀል በመፈረጅ “ ትልቅ ብርታት አሳይቷል” - ባለሙያ
የአልጄሪያ መንግሥት የፈረንሳይን የቅኝ ግዛት ታሪክ በወንጀል በመፈረጅ “ ትልቅ ብርታት አሳይቷል” - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.01.2026
ሰብስክራይብ

የአልጄሪያ መንግሥት የፈረንሳይን የቅኝ ግዛት ታሪክ በወንጀል በመፈረጅ “ ትልቅ ብርታት አሳይቷል” - ባለሙያ

አልጄሪያ የወሰደችው ይህ ውሳኔ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት “የቅኝ ግዛት ታሪክን ብቻ ሳይሆን የወቅቱን የቅኝ አገዛዝ መልክ እንዲቀይሩ” ሊያነሳሳቸው እንደሚገባ ካሜሩናዊው ጠበቃ ቫሌሬ ሜባራ ንዶንጎ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የትምህርት ሥርዓቱ፣ ቋንቋው፣ ባሕሉ እና አጠቃላይ ኢኮኖሚው “አሁንም የአፍሪካ ሀገራትን በኢምፔሪያሊዝም እና በቅኝ ግዛት ጥገኝነት ውስጥ እንዲቀሩ እያደረጋቸው ነው” ሲሉ ጠቁመዋል።

ጠበቃው አክለውም የከሰሃራ በታች አፍሪካ ሀገራት የሕግ ሰነዶች ሳይቀሩ “የፈረንሳይ ሕጎች ግልባጮች” መሆናቸውን በመጥቀስ፤ ይህንን የቅኝ ግዛት አሻራ ማሸነፍ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

ንዶንጎ፤ የቀድሞ ገዥ ሀገራት “አሁን ነጻ የወጡ የቀድሞ ተገዥ ሀገራትን ዝቅ አድርጎ ማየት ሊያቆሙ ይገባል” ብለዋል።

“ለጋራ ተጠቃሚነት ሲባል በትብብር መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ሊረዱ ይገባል” ሲሉ ጠበቃው ሞግተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0