የአፍሪካ ሀገራት የአሜሪካን የቬንዙዌላ ጥቃት ኮነኑ
18:43 03.01.2026 (የተሻሻለ: 18:44 03.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሀገራት የአሜሪካን የቬንዙዌላ ጥቃት ኮነኑ
ደቡብ አፍሪካ፦ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ኃይል አጠቃቀም "የዓለም አቀፉን ሥርዓት መረጋጋት እና በሀገራት መካከል ያለውን የእኩልነት መርህ የሚሸረሽር ነው" ብሏል።
ቡርኪና ፋሶ፦ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካን ድርጊት "በጽኑ በማውገዝ"፤ ድርጊቱ "የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተርን መሠረታዊ መርሆች የሚጥስ እና የላቲን አሜሪካና የካሪቢያን የሰላም ቀጣናን የሚያውክ ነው" ማለታቸውን ካራካስ ሚኒስትሩን ጠቅሳ አስታውቃለች።
ናሚቢያ፦ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይትዋ ሁኔታውን እየተከታተሉ እንደሆነ ጠቅሰው፤ በሕዝባችን ላይ የተፈጸመውን የወንጀል፣ የፈሪ እና ሕገ-ወጥ ወታደራዊ ጥቃት መሉ በመሉ ውድቅ እናደርጋለን" ማለታቸውን ካራካስ ገልጻለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X