በአሜሪካ የቬንዙዌላ ጥቃት ዙሪያ እስካሁን የታወቁ መረጃዎች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአሜሪካ የቬንዙዌላ ጥቃት ዙሪያ እስካሁን የታወቁ መረጃዎች
በአሜሪካ የቬንዙዌላ ጥቃት ዙሪያ እስካሁን የታወቁ መረጃዎች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.01.2026
ሰብስክራይብ

በአሜሪካ የቬንዙዌላ ጥቃት ዙሪያ እስካሁን የታወቁ መረጃዎች

🟠 አሜሪካ የቬንዙዌላን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በመወሰን ረገድ ተሳትፎ እንደምታደርግ ትራምፕ አስታውቀዋል።

🟠 ማዱሮ እና ባለቤታቸው በሄሊኮፕተር ከቬንዙዌላ እንዲወጡ ተደርገው ወደ ኒው ዮርክ በሚወስዳቸው መርከብ ላይ መሳፈራቸውን ትራምፕ ተናግረዋል።

🟠 የቬንዙዌላው ፕሬዚዳንት በአሜሪካ ፍርድ ቤት ቀርበው የወንጀል ክስ እንደሚመሰረትባቸው ሴናተር ማይክ ሊ፤ ሩቢዮን ዋቢ በማድረግ ይፋ አድርገዋል።

🟠 ቬንዙዌላ መብቷን በሁሉም ዓለም አቀፍ መድረኮች እንደምትከላከል እና ለዚህም ያሉትን ሁሉንም አማራጮች እንደምትጠቀም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

🟠 አሜሪካ በቬንዙዌላ ላይ በሰነዘረችው ጥቃት ወታደራዊ አባላት እና ሲቪሎች መገደላቸውን ምክትል ፕሬዚዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ ገልጸዋል።

🟠 የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፤ ከዴልሲ ሮድሪጌዝ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት፤ የጥቃት ወረራ ለተቃጣበት የቬንዙዌላ ሕዝብ ያላቸውን አብሮነት መግለጻቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

🟠 ነዋሪዎች የአሜሪካን ጥቃት ለመቃወም እና ለፕሬዚዳንት ማዱሮ ድጋፋቸውን ለመግለጽ በቬንዙዌላ አደባባዮች ወጥተዋል።

🟠 አሜሪካ ለሁለተኛ ዙር ጥቃት ዝግጁ የነበረች ቢሆንም ጥቃቱ ግን አስፈላጊ ሆኖ እንዳልተገኘ ትራምፕ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0