በአዲስ አበባ በቀን ከ300 ሺህ እስከ 500 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ሀገር አቋራጭ ተርሚናል ሊገነባ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአዲስ አበባ በቀን ከ300 ሺህ እስከ 500 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ሀገር አቋራጭ ተርሚናል ሊገነባ ነው
በአዲስ አበባ በቀን ከ300 ሺህ እስከ 500 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ሀገር አቋራጭ ተርሚናል ሊገነባ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.01.2026
ሰብስክራይብ

በአዲስ አበባ በቀን ከ300 ሺህ እስከ 500 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ሀገር አቋራጭ ተርሚናል ሊገነባ ነው

የዘመናዊ ተርሚናሉ ዲዛይን ነባሮቹን ትልቅና ትንሽ መናኸሪያዎች በማጣመር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ "አውቶብስ ተራ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለመገንባት ዝግጅት ላይ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።

​ ባለ አራት ወለል ሕንፃ የሚኖረው ይህ ተርሚናል፤ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን፣ የንግድ ሱቆችን፣ ቢሮዎችንና ሰፋፊ የመሳፈሪያ ቦታዎችን እንደሚይዝ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በረኦ ሀሰን ተናግረዋል።

ተርሚናሉ ከ15 የፈጣን አውቶብስ ኮሪደሮች እና ከባቡር መንገድ ጋር በድልድይ የሚገናኝ በመሆኑ፤ ዜጎች ከተርሚናሉ ሳይወጡ ወደ ሚፈልጉት አቅጣጫ መጓዝ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል ማለታቸውንም የሀገረ ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0