ደቡብ አፍሪካ በቬንዙዌላ ላይ የተፈጸመውን የአሜሪካ ጥቃት አወገዘች
17:50 03.01.2026 (የተሻሻለ: 17:54 03.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ በቬንዙዌላ ላይ የተፈጸመውን የአሜሪካ ጥቃት አወገዘች
የደቡብ አፍሪካ ዲፕሎማሲ፤ አሜሪካ በቬንዙዌላ እና በሀገሪቱ መሪ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ላይ በሰነዘረችው "ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት" እንዲሁም ፕሬዚዳንቱ ከባለቤታቸው ጋር በቁጥጥር ሥር ውለው ከሀገር እንዲወጡ መደረጋቸውን ተከትሎ "ከፍተኛ ስጋቱን" ገልጿል።
"ደቡብ አፍሪካ እነዚህ እርምጃዎች፤ ሁሉም አባል ሀገራት በማንኛውም ሀገር የግዛት አንድነት ወይም የፖለቲካ ነጻነት ላይ ኃይል ከመጠቀም ወይም ዛቻ እንዲቆጠቡ የሚደነግገውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር በግልጽ የጣሱ አድርጋ ትመለከታቸዋለች" ሲል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
እንዲህ ዓይነቱ የኃይል አጠቃቀም "የዓለም አቀፉን ሥርዓት መረጋጋት እና በሀገራት መካከል ያለውን የእኩልነት መርህ የሚጎዳ ነው" ሲልም አክሏል።
ደቡብ አፍሪካ ጉዳዩን ለመመርመር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጠይቃለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X