የገቢዎች ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግብር አሰባሰብን ለማዘመን ተስማሙ
17:40 03.01.2026 (የተሻሻለ: 17:44 03.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግብር አሰባሰብን ለማዘመን ተስማሙ
ተቋማቱ የተፈራረሙት ስምምነት የታክስ አሰባሰብ ስርዓቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል።
የዲጂታል ክፍያ ስርዓቱ ታክስ ከፋዮች ወደ ማዕከል ሳይመጡ ካሉበት ቦታ ሆነው በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ክፍያ መፈጸም የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
ስምምነቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ዘመናዊና የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት ለመዘርጋት እንደሚያስችል ተጠቅሷል።
በዚህም የሀገሪቱን የግብር አሰባሰብ ስርዓት ደህንነቱ የተጠበቀና ለልማት ምቹ በማድረግ ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመፍጠር ያግዛል ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X