የ ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030’ ስትራቴጂን ለማሳካት ዘመናዊ የሥልጠና ፕሮግራሞች ተጀመሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየ ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030’ ስትራቴጂን ለማሳካት ዘመናዊ የሥልጠና ፕሮግራሞች ተጀመሩ
የ ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030’ ስትራቴጂን ለማሳካት ዘመናዊ የሥልጠና ፕሮግራሞች ተጀመሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.01.2026
ሰብስክራይብ

የ ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030’ ስትራቴጂን ለማሳካት ዘመናዊ የሥልጠና ፕሮግራሞች ተጀመሩ

በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋ የተደረገውን የ “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂ ለማሳካት፤ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዘመናዊና ልዩ የሥልጠና ፕሮግራሞችን መጀመሩን አስታውቋል።

ሥልጠናው በተለይ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ከፍተኛ ብቃት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት ያለመ ነው ተብሏል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር፤ ተመራቂዎች በዘመናዊው የዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ሥርዓተ-ትምህርቱ በከፍተኛ የዲጂታል ክህሎቶች ላይ ትኩረት አድርጓል ብለዋል።

ኢንስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የመማሪያ አካባቢ ለመፍጠር ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን እያሟላ እንደሚገኝም ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0