የኢትዮጵያን የብልፅግና፣ ሰላም እና የኢኮኖሚ ፍላጎት ለማሟላት በርበራ እና ሌሎችን ወደቦችንም መቃኘት አስፈላጊ ነው - የዲፕሎማሲ እና ፖለቲካ ታሪክ ምሁር
15:55 03.01.2026 (የተሻሻለ: 16:04 03.01.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያን የብልፅግና፣ ሰላም እና የኢኮኖሚ ፍላጎት ለማሟላት በርበራ እና ሌሎችን ወደቦችንም መቃኘት አስፈላጊ ነው - የዲፕሎማሲ እና ፖለቲካ ታሪክ ምሁር
ሀገሪቱ ከያዘችው ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት እና እየጨመረ ከመጣው ፍለጎቷ አንፃር በጅቡቲ ወደብ ላይ ብቻ ተገድባ መቅረት አትችልም ሲሉ የኢትዮጵያ ልዑክ በቅርቡ በሶማሊላንድ በርበራ ወደብ ያደረገውን ጉብኝት አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን የሰጡት የጂማ ዩኒቨርስቲ መምህር በላይ በየነ ተናግረዋል።
ይህ ጠንካራ የመንግሥት እርምጃ በአኅጉሪቱ እና በአፍሪካ ቀንድ የኢትዮጵያን ጥቅም እና የፖለቲካ ፍላጎት ዳግም የሚበይን ነው ብለዋል።
"ኢትዮጵያ አሁን የብልጽግና ፍላጎቷንና ግቦቿን ለማሳካት እየሠራች ነው። ስለዚህ የበለፀገችና ያደገች ኢትዮጵያ የመፍጠር ራዕይን ለማሳካት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የኢንዱስትሪና የልማት ኮሪደሮችን ማቋቋም በጣም አስፈላጊ ነው። ለዚህ ወደቦችን ማሳደግና በርበራ ወደብን መጠቀም ያስፈልጋል። የበርበራ ወደብ በጣም ተስማሚና ምቹ ነው።"
ምሁሩ በቀጣናው የተለያዩ ሀገራት ፍላጎት አየጨመረ መምጣቱን በማንሳት፤ ኢትዮጵያም በአፍሪካ ያላትን የላቀ ቁመና መጠቀም እንዳለባት ጠቁመዋል።
"ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላት ትልቅ ሚና የማይካድ ነው። ስለዚህ የተለያዩ ወደቦችን መጠቀም በአጠቃላይ በአፍሪካ ያለንን ጂኦፖለቲካዊ ፍላጎት በእጅጉ ያስጠብቃል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኃይል ሚዛንን መጠበቅ የምትችል በጣም ስትራቴጂካዊ እና ተሰሚ ኃይል መሆን አለባት።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X