ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች
ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.01.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች

የ2029ኙን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ፍላጎቷን አሳይታ የነበረችው ሀገሪቱ፤ ውድድሩ በአንድ ዓመት ቀድሞ የሚካሄድ በመሆኑ ጥያቄዋን አሻሽላ ይፋዊ ጥያቄ ለካፍ ማስገባቷን የፌዴሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ባህሩ ጥላሁን ተናግረዋል።

ይህ ጥያቄ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ ከ2028 ጀምሮ የአፍሪካ ዋንጫ በየአራት ዓመቱ እንዲካሄድ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ የመጣ ነው።

ኢትዮጵያ የስታዲየም መሠረተ ልማቶች ላይ ትኩረት ሰጥታ ለውድድሩ የሚመጥኑ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየሠራች እንደምትገኝም ተገልጿል።

የ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ በምስራቅ አፍሪካ ዞን በኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ኬንያ በጣምራ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0