የደቡብ የመን ተገንጣዮች ‘ነጻ የደቡብ አረቢያ’ የተሰኘ ሕገ-መንግሥት አፀደቁ

ሰብስክራይብ

የደቡብ የመን ተገንጣዮች ‘ነጻ የደቡብ አረቢያ’ የተሰኘ ሕገ-መንግሥት አፀደቁ

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንደሚደገፉ የሚነገርላቸው የየምን ተገንጣዮች፤ ከአንድ ቀን በፊት በሳዑዲ አረቢያ በሚደገፉ ኃይሎች ላይ ጦርነት ማወጃቸው ተዘግቧል።

ተገንጣይ ኃይሎቹ በታኅሣሥ ወር የሀድራማውት እና የማህራ ምስራቃዊ ግዛቶችን በቁጥጥራቸው ሥር ማዋላቸው ይታወሳል።

የሰነዱ ዋና ዋና ድንጋጌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

የደቡብ አረቢያ መንግሥት ኤደንን ዋና ከተማዋ በማድረግ ሙሉ በሙሉ ሉዓላዊና ነጻ ሀገር መሆኗ ታውጇል።

የሀገሪቱ ድንበር ቀደም ሲል ዓለም አቀፍ ውቅና በነበረው የየመን ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (የቀድሞዋ ደቡብ የመን) ድንበር መሠረት ይሆናል።

ደቡብ አረቢያ የአረብ እና የእስልምናው ዓለም አካል ነች፤ አረብኛም ብሔራዊ ቋንቋዋ ይሆናል።

እስልምና የሀገሪቱ ሐይማኖት እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን የእስልምና ሸሪዓ ሕግ ደግሞ ዋነኛው የሕግ ምንጭ ይሆናል።

ሕጋዊ ግዴታዎችን ለማሟላትና የመንግሥት ተቋማትን ለማዋቀር የሁለት ዓመት የሽግግር ወቅት ተደንግጓል።

ሌሎች የየመን የፖለቲካ ኃይሎችም ሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የየመን መንግሥት እስካሁን ለጉዳዩ የሰጡት ምላሽ የለም።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየደቡብ የመን ተገንጣዮች ‘ነጻ የደቡብ አረቢያ’ የተሰኘ ሕገ-መንግሥት አፀደቁ
የደቡብ የመን ተገንጣዮች ‘ነጻ የደቡብ አረቢያ’ የተሰኘ ሕገ-መንግሥት አፀደቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.01.2026
አዳዲስ ዜናዎች
0